እያለን አይመስልም?
የቀናት ፈጣሪ ቢጠይቀን ጊዜን እራሱ የሰጠንን
ሊነግረን ሊያሳየን ቢፈልግ በቃሉ የሚፀየፈውን
ተገኝ በጓዳህ ተውና መባከን አንብብ ቅዱስ ቃሌን
በአገልግሎት ስም ብዙ ወጣህ ወረድክ ሳትሰጠኝ ልብህን
ባልንግጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ያልኩትን አቃለህ
በአንፃሩ ጥላቻ ቅናት ሃሜት ቂምን በሙሉ ተሞልተህ
አመልክሃለው አትበል በደም የረከሱ እጆችህን አንስተህ
ያላልኩትን ይላል እያልክ በድፍረት
ሃብት ዝና ለማትረፍ ለስጋህ በውሸት
ስሜን ዘበትክበት ንቀትህ ልክ አጣ
ምን ያስገርምሃል ልቀጣስ ብመጣ
ለፍቅሬ መጠን ወደር ስለሌለው
ህዝቤ ሆይ ተመለስ ተመለስ እልሃለው
ማስመሰል ይቻላል የአምልኮ መልክ ይዞ ሀይሉን ግን መካድ
በአምላክ ስም መነገድ ቀድሞውንም ሳይሆኑ በእውነቱ መንገድ
አልፈለኩምና የአደባባዩን
የመድረኩን ውበት ጋጋታ ጩኸቱን
አትፈልጉኝ በዚያ በሌለሁበት
ቅዱሱንም ስሜን በከንቱ አትጥሩት
ይልቅስ ይብቃችሁ ማስመሰል ሳትሆኑ ደቀ መዝሙሬ
ያስከፍላል ዋጋ በጠባቡ መንገድ መሄድ ከዋላዬ
በከንቱ ውዳሴ ስሜን አታባክን
ወደ እልፍኝህ ግባ ዝጋና በርህን
ከእኔ ተማር በፃፍኩት ቃሌ ላይ መሆን ያለብህን
ከመስዋዕትህ በፊት የሚያስደስተኝን
ልብ ብለህ ስማኝ ስጠኝና ልብህን
ከመናገር ይልቅ ማዳመጥን ምረጥ አትከራከረንኝ
ለከሌ ነው አትበል እራስህን ፈትሽ ወድሃልሁ ካልከኝ
ለሁሉም ጊዜ አለው እንደሚለው ቃሌ
በግል በቤትህ ቅረብ ወደ እኔ
የሚሰማኝ እኮ በእርጋታ ይቀመጣል
ከመከራም ስጋት በእኔ ውስጥ ያርፋል
ከፀሃይ በታች አዲስ ነገር የለም ሌላኛው ይመጣል
ስለዚህ ፍጥረቶቼ ልባችሁን ስጡኝ
አይኖቻችሁም ደግሞ ይውደዱ መንገዴን
ለምን ይሄ ሆነ ብላችሁ አትሙኝ
ክፉዘመናትን እየዋጃችሁ እኔን አስከብሩኝ
እያለን አይመስልም? ቅዱን አምላካችን
ስለ አዲሱ ክስተት(COVID 19) በአፅንኦት ካስተዋልን
አቤቱ ሁላችንን እግዚአብሄር ይርዳን
ልባችንን እንስጥ ለፈጣሪያችን።
ተባረኪ