ለስራና ለልዩ ልዩ ነገሮች ስንሮጥ ራሳችንን እንጥላለን። ከሁሉ በፊት ግን ቤተመቅደስ የሆነውን አካላችንን መንከባከብ እጅግ ማስተዋል ነው። ፈውስ ከራስ ይጀምራል። ራሳችንን ብንጠብቅ ለሌላውም በተሻለ ሁኔታ መትረፍ እንችላለን። ራሴን ሳየው ጉድለቴ የመጣው ስለዚህ ጉዳይ የሚገባውን ትኩረት ካለመስጠት ይመስለኛል። አሁን ግን ነቅቻለሁ። ሰይጣን አሩጦ አሩጦ የበሽታ አደጋ ላይ ሊጥለን ይፈልጋል። ረጋ ብሎ ራስን መንከባከብ እጅግ ደስ ይላል። ይህን ጉዞ ከጀመርኩ ሩቅ አይደለም። ይህ አካሄድ የዕድሜ ልክ እንዲሆን ፀሎቴ ነው። ገና ብዙ ይቀረኛል፥ ግን ትኩረቴ ክብደት መቀነስ ላይ ብቻ ሳይሆን ይህ ኑሮ ፀባዬና ዐመሌ እንዲሆን እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ቁምነገሩ ክብደት መቀነስ ብቻ ሳይሆን በዚያው ፀንቶ መኖሩ ነው። በፊቴ ያለው ጎዳና ከባድ ቢመስልም በጌታ ፀጋ ይቻላል። ይህን ጉዞ ብቻዬን ከምሄድ ከምወዳቸው ወገኖቼ ጋር በአብሮነት እንድንጓዝ ይህን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ራስን መጠበቅ ምግብ አመጋገብና እንቅስቃሴ (ስፖርት) ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ ዕረፍት መውሰድ፥ ጥሩ የእንቅልፍ ልማድ፥ ውሀ መጠጣት፥ መዝናናት የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ቤተመቅደሳችንን ሁሉ አቀፍ ጤናማ እንዲሆን መንከባከብ ይገባናል። መንፈሳዊነት ይህንን ይጨምራል ከማለት ይልቅ፥ ከዚህ ይጀምራል ብንል አቅም እናገኛለን። አገልግሎታችን ቤተመቅደሳችንን ከመጠበቅ ቢጀምር አባታችን እጅግ ደስ እንደሚለው ገብቶኛል። እኛ ራሳችንን መጠበቃችን ደስ የሚያሰኘው እውነተኛ አባት ለሆነን እግዚአብሔር ክብር ይሁንለት። እናንተም በዚህ ረገድ ምስክርነት ካላችሁ አካፍሉ። አንዳችን ከሌላው መማር እንችላለን። አንዳችን ለሌላው መነቃቃት እንሆናለን። እኔም እያደረኩ ያለሁትን በዝርዝር አካፍላችዋለሁ። የእግዚአብሔር ረድሄትና በረከት ከእያንዳንዳችን ጋር ይሁን።
top of page
bottom of page
ልክ ነው የጌታ ቤተ መቅደስ እንደመሆናችን ራሳችንን መጠበቅ በራሱ ጌታን መታዘዝ ነው። ራስን መጠበቅ ራስን መግዛት ነው የምፈልገውን ነገር ግን የማይጠቅመኝን ስለፈለኩ ብቻ የማደርግ ከሆነ ለምሳሌ የምፈልገው ምግብ ለጤና መጥፎ እንደሆነ እያወቅሁ በግድ የለሽነት ለፍላጎቴ ከተሸነፍኩ ራሴን እየገዛሁ እንዳልሆነ አስተውላለሁ ባጠቃላይ የጌታ ቤተ መቅደስ የሆነውን አካላችንን ከሚያበላሹ ሁሉ መጠበቅ ሃላፊነታችን ነው በዚህም ደግሞ የሚከብረው ቤተ መቅደሱ ያረገን ጌታ እግዚአብሔር ነው እኔም የጌታን ቃል እያሰላሰልኩ ዋክ ማረግ ጀምሬያለሁ እንዲሁም ጤናን እንቅልፍን ከሚያውኩ ከማያንፁ ወሬዎች ራሴን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነው። ልምድህን ስላካፈልከን ጌታ ይባርክህ ክብር ሁሉ ለእግዚአብሄር ይሁን አሜን።
ጌታ ይባርክህ! እኔም ይህን ተረድቼ ዎክ ጀምሬያለሁ:: በዛውም የጥሞና ጊዜ አድርጌው ሁለት ወፍ በአንድ ድንጋይ ሆኖልኛል::